top of page

"ደሜን በመለገስ የወገኔን ህይወት እታደጋለሁ!"


የሞራል ልዕልና የሚታይበት ፣ የመንፈስ እርካታ የሚገኝበት ፣ የህዝባችን የመረዳዳት እሴቶች የሚጎለብቱበት ፣ ወንድማማችነትና እህትማማችንት የሚጠብቅበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመዲናችን አዲስ አበባ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካሞችን እና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ዜጎችን በጉልበት ፣ በገንዘብ ፣ በእውቀት በመደገፍ ፣ ከጉስቁልና ህይወት እንዲወጡ እና "ወገን አለን " የሚል ተስፋ እንዲሰንቁ እያስቻለ ይገኛል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሚዎችም በሚደረጉላቸው ድጋፎች እራሳቸውን ቀይረው እነሱም በተራቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች የሚሆኑበት ዕድል ሰፊ ነው።

የከተማችን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቀዛቅዞ ከነበረበት እንዲያንሰራራ እና ተቋማዊ እንዲሆን በከተማ አስተዳደሩም ልዩ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ እና ሌሎች ተቋማትና አደረጃጀቶችም የማስተባበር ሚናቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት በቤት እድሳት፣ በማስተማር ፣ በጤና ተቋማት በሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ በችግኝ ተከላ ፣ በትራፊክ አገልግሎት እና በመሳሰሉት የከተማችንን ወጣቶች በማስተባበር ጭምር በጋም ክረምትም እየተረባረቡ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በዛሬው ዕለት ደግሞ "ደሜን በመለገስ የወገኔን ህይወት እታደጋለሁ!" በሚል መሪ ቃል 1000 የክንፉ አመራሮችና አባላት የተሳተፉበት ከተማ አቀፍ የደም ልገሳ ፕሮግራም አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የወጣቶች ክንፍ የከተማችን ወጣቶች ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ፣ ወጣቶችም ለከተማችንና ለሀገራችን የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዲችሉ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የከተማችን ወጣቶች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መጠናከር እየተደረገ የሚገኘው ጥረት በወጣቶች ዘንድ የትብብር ፣ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ስሜትን ከፍ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

አንድ ሺህ ወጣቶች የተሳተፉበት የዛሬው የደም ልገሳ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በደም ማጣት የሚሞቱ እናቶቻችንን ህይወት ለመታደግ ያስችላል ያሉት ወጣት መለሰ በቀጣይም በክ / ከተሞች እና በወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ወጣቶች በከተማችን የልማት ስራዎችም የሚያደርጉትን ብርቱ እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ክንፉ የሚያደርገውን ርብርብ እንደሚያጠናክርም ወጣት መለሰ ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት


 
 
 

Comments


bottom of page