የድህረ እውነት ዘመን በእውነትና በእውቀት በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች፣ ስራ አስፈፃሚዎችና አባላት ስልጠና ተሰጠ
- addis ketema Sub city
- Jul 1
- 1 min read
፡በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብነት አሰግድ ያለንበት ወቅት የሚዲያ ቴክኖሎጂ እድገት በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋበት በመሆኑ ቴክኖሎጂን በእውቀትና በእውነት መምራትና ማስተዳደር እንደሚገባ ገልፀዋል። በድህረ እውነት ዘመን አፍራሽ ሃይሎች ሆን ተብሎ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድነትና ወንድማማችነት/ እህትማማችነት እሴት ለማፍረስ እየሰሩ በመሆኑ በእውነትና በእውቀት መመከት ይገባል ብለዋል፡፡በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ያሬድ ተፈራ በበኩላቸው በዚህ በድህረ እውነት ዘመን ውሸት በዕውነት ላይ የበላይነትን ለመጎናፀፍ ብርቱ ትግል የሚያደርግበት ዘመን በመሆኑ እንደ ፓርቲ አባል ብሎም እንደዜጋ እውነትን መሠረት በማድረግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ብርቱ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል።በተለይም ደግሞ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ሀሰተኛ መረጃዎች እንደ ልብ በስፋት በሚሰራጩበትና ማህበራዊ ሚዲያውን ተቆጣጥረው ህዝብን ከህዝብ ሀይማኖትን ከሀይማኖት ለማጋጨት በሚሰሩበት ጊዜ ወጣት አባላት በየአከባቢው ያሉንን እውነት ተጠቅመን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞችና ሜንስትሪም ሚዲያው መረጃዎች ለህዝብ የማድረስና ግልፅነት የመፍጠር ስራ መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ስልጠናውን የወሰዱ ሰልጣኞች በስልጠናው የተገኘውን እውቀት ካለን አቅም ጋር በማስተሳስር የበለጠ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡










Comments