top of page

ወጣቶች ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን በበጋ ወራት በተሰሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በተግባር አቅማቸውን የገለጡበት ለማህበረሰቡ መለወጥ የተጉበት አመት ነው!!


በዛሬው ዕለት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የ2017 በጀት አመት የበጋ በጎ ፈቃድ አፈፃፀም የጋራ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ወረዳዎችና ተቋማት እውቅና ሰጥቷል። ወጣት ያሬድ ተፈራ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ለተቋማት ከተሰጡ እውቅናዎች መካከል የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት አንዱ ሲሆን በበጋ በጎ ፈቃድ ሙሉ ቤት እድሳት 48 ፣ማዕድ ማጋራት 3482 ፣ደም ልገሳ 3922 ዩኒት ፣በጎነት በሆስፒታል ፣የፅዳት ዘመቻ እና ችግኝ እንክብካቤ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ወጣት ያሬድ ተፈራ ገልፀዋል። ሃላፊው በገለፃቸው በዚህ ተግባር ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ የክንፉ አመራርና አባላት እንዲሁም ወጣት ባለሀብቶችን አመስግነው በተሰጠን እውቅና ይበልጥ በመነሳሳት በቀጣይ በጀት አመት ከክረምት በጎፈቃድ ንቅናቄ ጀምሮ የዜጎችን ሂዎት የሚቀይር ሰባዊ ስራ በመስራት የበጠ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።


 
 
 

コメント


bottom of page