top of page

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብና አደረጃጀት ዙሪያ ለወጣቶች ክንፍ ኮሚሽን አመራሮች ስልጠና ሰጥቷል።


የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤት የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና አደረጃጀት አስመልክቶ ከሁሉም ወረዳ ለተውጣጡ የኮምሽኑ ወጣት ክንፍ አመራር ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮምሽን ጽ/ቤት ኮምሽነር አቶ ሙሉሰው ደስታ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና አደረጃጀት ሰነድ ለወጣት ክንፍ አመራር የማሳወቅ፣ የማስገንዘብ እና የማስረፅ ተልዕኮ በማገብ፣ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የሚጠበቅባችሁን ግዴታ ከመወጣት አንፃር ውስጠ ፓርቲ አሠራሮችን በጥንቃቄ እንድትፈጽሙ ያግዛል ሲሉ ገልፀው ፣ የፓርቲ እሴትን በማስፈን ህብረ ብሔራዊ አንድነት እና ወንድምማማችነትና እህትማማችነትን በህብረቱ ውስጥ እንዲኖር ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ። ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጡት ግንዛቤ ለወጣት ክንፉ አደረጃጀት መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚደርግ በመሆኑ ለሁሉም አባላት ተደራሽ የሚያደርጉ መሆኑን ገልጸዋል ።


 
 
 

Comments


bottom of page