top of page

የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ወጣቱ የሚጠበቅበትን ሚና

የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ወጣቱ የሚጠበቅበትን ሚና መወጣት ያስፈልጋል

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ፓርቲው በጉባኤው ካስቀመጣቸው አንኳር ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች አንዱ የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑንም ገልፀዋል። የወጣቶች ክንፍም የጉባኤውን ውሳኔዎች ተቀበሎና አምኖ የወጣቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ዋነኛ አላማ አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ከወጣቶች ለተነሱ ጥያቄዎች የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ አባል ወጣት ያሬድ ተፈራ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ወጣቱ የሚጠበቅበትን ሚና መውጣት ያስፈልጋል ብለዋል ወጣት ያሬድ ተፈራ። ወጣቱ በሠላም ግንባታ ላይ ሁሌም ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት ወጣት ያሬድ ወጣቱ በሀሳብ የበላይነት እና ግጭቶች በውይይት እንደሚፈታ የሚያምን መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ወጣቶች ከመንግሥት ጎን በመቆም የልማት አርበኛ መሆን አለባቸው ያሉት ወጣት ያሬድ የስራ ተነሳሽነታቸውንም ባህል በማድረግ ሌሎች አርዓያ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወጣት ወገንህ ወርቅነህ በበኩላቸው ፓርቲያችን ብልፅግና ለወጣቱ ያለው ሚና የላቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።


 
 
 

Comentários


bottom of page