የድሬዳዋ ወጣቶች በአዲስ ከተማ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ::
- addis ketema Sub city
- 32 minutes ago
- 1 min read
የድሬደዋ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ጋር የልምድ እና ተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል።የተደረገው የልምድ ልውውጥ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖርና የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ከድሬዳዋ የትንሿ ኢትዮጵያ ማሳያ ወደ ሆነችው አዲስ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት አቶ መለሰ አባተ በበኩላቸው የተደረገው ልምድ ልውውጥ በተቀራራቢ አቅም ጠንካራ የወጣት አደረጃጀት በመፍጠር የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚጠቅም ነው ብለው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክፍል እንደ ከተማ የተሻለ የተግባር ተሞክሮ ያለው እንደሆነም ገልፀዋል፡፡የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ያሬድ ተፈራ በበኩሉ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ክንፍ የፓርቲውን መዋቅር ለማጠናከር ከሚያከናውናቸው መደበኛ ተግባራት በተጨማሪ ተሞክሮ የሚሆኑ፥ የህብረተሰቡን ችግር ሊያቃልሉ በሚችሉ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡በተደረገው ልምድ ልውውጥ በርካታ ተሞክሮዎችን እንደቀሰሙ የተናገሩት የድሬድዋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት አቶ ሙኸዲን አብዱራህማን በልምድ ልውውጡ የተገኙ ተሞክሮዎች ተግባራዊ በማድረግ የድሬደዋ ከተማ ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገልፀዋል ። የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች ከልምድ ልውውጡ በኋላ "በጎነት በሆስፒታል" በተሰኘው መርሃ-ግብር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስቲታል በመገኘት ህሙማንን ጠይቀዋል፡፡



























Commentaires