የአዲስ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከአይሲቲ አገልግሎት ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን 2 አዲስ የበለጸጉ ሲስተሞችን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ፡፡
- addis ketema Sub city
- May 26
- 1 min read
የአዲስ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አይሲቲ አገልግሎት ዘርፍ አዲስ የለሙ የብልጽግና ፓርቲ እጩ አባል በኦን ላይን የመመልመል እና ሁሉንም ስራዎች ወደ አንድ አደረጃጀት የማምጣት ስራ እና የአባላት ቅሬታ መከታተያ ሲስተም ስራ ማስጀመሩን አስታዉቋል፡፡በዚህ የሲስተም ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ እንደተናገሩት የፓርቲን ስራዎች የተሻለና ቀልጣፋ እንዲሁም ተአማኒ ለማድረግ ቴክኖሎጂን መጠቀም የማይተካ ሚና እናዳለዉ ጠቁመዉ እንደ ክፍለ ከተማ በዚህ አመት ከያዝናቸዉ ዋና ዋና እቅዶች አንዱ የተለያዩ በማኑዋል ሲሰሩ የነበሩትን ተግባራት በቴክኖሎጂ አስደግፈዉ መምራት አንዱ ነዉ ያሉ ሲሆን ይህንንም ተግባር በቀጣይ አጠናክረን የሚንቀጥል ነዉ ብለዋል፡፡የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አይሲቲ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወገን ካሳሁን በበኩላቸዉ ዘርፉ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራቶች አንዱና ዋነኛዉ የተለመደዉን የማኑዋል ተግባር በማስቀረት የፓርቲን ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ማስቻል አንዱ ነዉ ያሉ ሲሆን የነዚህም ሲሰተሞች አላማ ከዚህ በፊት የነበረዉን የማኑዋል ስርዓት በመቀየር የፓርቲን ተግባራት ኦንላይን በማድረግ የተሻለና ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻል ነዉ ያሉ ሲሆን ዛሬ ይፋ የተደረጉት ሲስተሞች የነበሩትን ችግሮች እንደሚቀርፉ ጠቁመዉ በቀጣይም የሲስተም ልማትና ሌሎች የፓርቲን ስራ ዘመን ባፈራቸዉ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ታግዘዉ እንዲሰጡ በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡






Comments