top of page

የአዲስ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሰዉ ተኮር ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

የአዲስ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሰዉ ተኮር ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ "ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴን እወጣለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ከአሙዲ ምገባ ማዕከል ጋር የአብሮነት ማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር አካሂዷል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የፓርቲ አሳቤን ለማስረፅ ብሎም የአባላቱን የተግባር ስምሪት የሚያጠናክሩ የንቅናቄ አጀንዳዎቹን በዕቅድ በመያዝ የ2ወር አጀንዳ ተኮር ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን በዛሬዉ እለትም የማዕድ ማጋራት አካሄዷል።

በፕሮግራሙ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ያሬድ ተፈራ እንዳሉት በኑሮ ደረጃ ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች የወጣቶች ክንፍ አባላት በሣምንታዊ ተግባሩ የተለያዩ የምግብ ግብዓት በማሰባሰብ በአሙዲ ምገባ ማዕከል የአብሮነት የማዕድ ምገባ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል ።

ወጣት ያሬድ ተፈራ በማከልም በቀጣይም በመሰል ተግባር ወጣቶችን በማስተባበር ድጋፍ የሚያደረግ መሆኑን ገልጸዋል ።


 
 
 

Comments


bottom of page