የአስተሳሰብ ጥራት ለሞዴል የብልፅግና ህብረት ግንባታ!!
- addis ketema Sub city
- May 26
- 1 min read
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ "የአስተሳሰብ ጥራት ለሞዴል የብልፅግና ህብረት ግንባታ!!" በሚል ርዕስ ለብልፅግና ወጣቶች ክንፍ የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢዎች የመጀመሪያ ዙር የአመራር ፈተና ሰጥቷል። የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ወጣት ያሬድ ተፈራ የፈተናው ዋና ዓላማ ባለፉት ጊዜያቶች "ከገዥ ትርክት እና የፓርቲያችን አሰራርና መመሪያ የተረዳ ወጣት አባሎቻችን ያላቸውን አቅም የክንፉ የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢዎች በአመራሩ ውስጥ ዕሳቤው ምን ያህል ሰርፆ እንደሚገኝ ለመመዘንና የማንበብ ባህሉን በማሳደግ ግዜውን የሚመጥን የወጣት አመራር ለመቅረፅ ያለመ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ከፈተናው በሗላ የወጣት አመራሮች የሚያመጡትን ውጤቶች መነሻ በማድረግ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑንና የአቅም ምዘና ፈተናዎች በየጊዜው በመስጠት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይ በየደረጃዉ ለሚገኙ የቤተሰብ አመራሮች በወረዳ እና በህብረት ደረጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።










👍