የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ይገኛል
- addis ketema Sub city
- May 26
- 1 min read
በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰዋል። አያይዘውም ፓርቲው ወጣቶችን በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ማህበራዊ መስኮች በግንባር ቀደምትነት እንዲሳተፉ እና ለውጡንም በባለቤትነት እንዲመሩት በማድረግ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ገልፀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አባንግ ኩመዳን በበኩላቸው የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማስፋት እንዲቻል በወጣት ክንፍ መሪነት ባለፉት 9 ወራት ሰፊ ስራዎች እንደተሰሩ አንስተዋል። በበጀት አመቱ በወጣቶች ክንፍ የተከናወኑ ተግባራት የፓርቲውን ስኬታማ ጉዞ የሚያመላክቱ እና ለታለመው ሁለንተናዊ ስኬትም አቅም እንደሆነም አክለዋል። በአፈፃፀም ግምገማ የተለዩ ጠንካራ ተሞክሮዎችን ለማስቀጠል፣ መልካም ልምዶችን ለመጋራትና ጉድለቶች ለማረም መድረኩ ምቹ ዕድል እንደፈጠረ ተጠቁሟል። የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ወጣት ሰብለ በቀለ የጽ/ቤቱን የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት አቅርብው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡ የግምገማ መድረኩም ለተከታታይ 2 ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።







Comments