"ወጣትነት ትልቅ የሀገር ጉልበት ነው" አቶ ፍስሐ ደሳለኝ
- addis ketema Sub city
- Jul 1
- 1 min read
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ሀገሬን እገነባለሁ ኀላፊነቴንም እወጣለሁ" በሚል መልዕክት ክልላዊ የወጣቶች ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው። በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሐ ደሳለኝ ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የማይተካ እና ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመት በፈተናዎች ውስጥ ኾና ውጤታማ ሥራዎችን መሥራቷን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የብልጽግና ግስጋሴ ሂደት ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ መኾኑንም ገልጸዋል። ያሰብነውን የብልጽግና ጉዞ ባሰብነው ፍጥነት እና ጊዜ ለማሳካት ፈተና እየኾነ ያለ የሰላም እጦት አለ ነው ያሉት። ነገር ግን ፈተናዎች ከብልጽግና ጉዟችን አያስቀሩንም ብለዋል። በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ወጣቶች ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መቆየታቸውን ያነሱት ኀላፊው አስተዋጽኦችሁ ከፍተኛ መኾኑን ተገንዝባችሁ ኃላፊነትን መወጣት ይገባችኋል ብለዋል።"ወጣትነት ትልቅ የሀገር ጉልበት ነው፣ እናንተ የሀገር ሀብት ናችሁ፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተመሥርቶ ነው" ብለዋል። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ብዙ ቀውስ አጋጥሟል ያሉት ኀላፊው ችግሩ እንዲቀለበስ እና ክልሉ ወደ ልማት እንዲገባ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍላችኋል ነው ያሉት። ቀጣይም ከዚህ የበለጠ መስዋዕትነት ይጠይቀናል፣ ትልቁ መስዋዕትነት የሚጠይቀው ድህነትን ለመዋጋት ነው ብለዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሚናቸው ከፍ ያለ መኾኑንም ገልጸዋል።ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡም አሳስበዋል። ሰላም ካለ ሁሉም ነገር በታሰበው ልክ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።ባለፉት ዓመታት በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች በክልሉ የጠፉ ሀብቶች አሉ ያሉት ኀላፊው የገጠሙ ችግሮችን ፈትተን፣ ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል ነው ያሉት። የክልሉን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ አሻጋሪ እና የቁጭት ዕቅድ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። አሻጋሪ እና የቁጭት ዕቅዱ ስኬታማ እንዲኾን ተልዕኳቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል። በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ እንዲኾኑም አሳስበዋል።ለሀገር እንቅፋት ከኾነ የተሳሳተ የሚዲያ ዘመቻ ራሳቸውን በማራቅ በትክክለኛ ሥራ ላይ እንዲሠማሩ ነው ያስገነዘቡት። ትክክለኛው መረጃ ለማስገንዘብ እና የተሳሳተውን መረጃ ለመቀልበስ ትልቅ ሚና እንዳላቸውም አሳስበዋል። ያላቸውን ታላቅ ሚና ተገንዝበው እንዲሠሩም አመላክተዋል።









留言