ከብሄርተኝነት ወደ ብሄራዊነት ገዢ ትርክት
- addis ketema Sub city
- May 27
- 1 min read
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ "ከብሄርተኝነት ወደ ብሄራዊነት ገዢ ትርክት" በሚል ርዕስ የስነ ፅሁፍ ምሽት አካሄደ። በስነ ፅሁፍ መሽቱ ላይ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ያሬድ ተፈራ፣የወረዳዉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ይማሙ ሙደሲር፣የወረዳዉ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ እታፈራሁ አይዳና እንዲሁም የወረዳዉ አመራሮችና እንግዶች ተገኝተዋል። በስነ ፅሁፍ ምሽቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ያሬድ ተፈራ ከሚያለያዩን ነጠላ ትርክቶች አንድ ወደ ሚያደርገን ብሄራዊ ትርክት መሸጋገር ለሃገራችን የብልፅግና ጉዞ ትልቅ ሚና እንዳለዉ ገልፀዉ የአድዋ ድል አባቶቻችን በአንድነት ቆመዉ ሃገራችንን ነፃ እንዳወጡ ሁሉ የአሁን ትዉልድ በልማት እና በተለያዩ ሃገራዊ ስራዎች ላይ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልፀዋል።
የካቲት 20/2017ዓ.ም








Comments