top of page

እውቀቴን ገንዘቤን እና ጉልበቴን ለወገኔ


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የብልጽግና ፖርቲ የወጣቶች ክንፍ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት አስጀመረ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ወጣት ያሬድ ተፈራ በበኩላቸው ወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ተቋም እንደመሆኑ መጠን በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለው በወረዳ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን ተሻግረውም ድጋፍና እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የመድረስ ሃላፊነትና ግዴታችን ነው ብለዋል::በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የወጣቶች ክንፍ ሀላፊ ወጣት ዮናስ ተቋሙ በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለው በዛሬው እለትም የአቅመ ደካማ ቤት ለማደስ መምጣታችሁ ቁርጠኛ የአመራር ተግባር ነው ብለዋል።

                      መጋቢት 02/2017ዓ.ም


 
 
 

Comments


bottom of page