"መልካም ልምዶችን በማስፋት የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግብአችን ዕውን እናደርጋለን! "
- addis ketema Sub city
- Jun 13
- 2 min read
የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ክ/ከተሞች ልምድ ለመለዋወጥ እና አንድነታቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩበት ነው - አቶ ሞገስ ባልቻ
"መልካም ልምዶችን በማስፋት የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግብአችን ዕውን እናደርጋለን! "በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪነት መልካም ልምዶችን ለማስፋት የሚያግዝ የፎቶ አውደ ርዕይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና አባላት በተገኙበት በድምቀት ተከፍቷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የፎቶ አውደ ርዕይው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና የጠራ ሀሳብ ይዞ፣ ታላቅ ህልም ነድፎ እየተጋ ፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል እየቀየረ ፣ በተግባር የተፈተሸ ድል እያስመዘገበ የሚገኝ ጠንካራ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ብልፅግና በሰው ሀይል አሰላለፉ፣ በእሳቤ ምጥቀቱ ፣ በተግባራዊነቱ ጠንካራነቱን ያስመሰከረ ፓርቲ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ህልማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና በመሆኑ አባላት እና አመራሩ ብዙ መትጋት እና ብዙ መልፋት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ሁሉም ክ/ከተሞች ስራዎቻቸውን በማቅረብ ልምድ በመለዋወጥ አንድነታቸውን በማጠናከር ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩበት መሆኑንም አስረድተዋል። ሰርቶ የማሰራት ባህልን ይበልጥ በማዳበር ፣ በተለየ ርብርብ ከተማችንን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር በቀጣይ 90 ቀናት ለሚኖሩ በርካታ ተልዕኮዎች አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አቶ ሞገስ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ብልፅግና ፓርቲ በውጤት የተገለጠ ሰፊ አቅም ያለው ፓርቲ መሆኑን ጠቅሰው አባላት የማይተካ ሚናቸውን አጠናክረው በመቀጠል ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል። አባላት ከብልፅግና ቤተሰብ ጀምሮ ባሉት ተቋማት ተሞክሮዎችን ሲለዋወጡ እንደቆዩ ያወሱት አቶ አብርሃም የተከናወኑ ተግባራትን በፎቶ ኤግዚቪሽን የጋራ ማድረግ መቻሉም ቅንጅታዊ ርብርብ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው ክ/ከተማው እውነተኛ ህብረ ብሔራዊነትን የሚያንፀባርቁ በርካታ ተቋማት እንደሚገኙበት ጠቁመው የህዝብ መሰረተ ልማቶችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። አሻጋሪ እሳቤዎችን ተግባራዊ ለማድረግ አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡ በማድረግ ፣ ህዝባችንን የልማት ሀይል እንዲሆን ተሳታዊነቱን በማሳደግ ለሁሉም ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። በፎቶ ኤግዚቢሽን ፕሮግራሙ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው እና ሌሎችም የከተማ ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም ክ /ከተሞች የመጡ አባላት ተሳትፈዋል። በፕሮግራሙ ላይ ሁሉም ክ/ከተሞች ባለፉት ወራት የተከናወኑ የፖለቲካና የድርጅት እንዲሁም የሰላምና የልማት ስራዎቻቸውን ያስጎበኙ ሲሆን ፤ ከየክ /ከተሞች የመጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም ህብረ ብሔራዊ አብሮነትን የሚያጠናክሩ ውብ ዝማሬዎችን አቅርበዋል። በማራኪው እና ታሪካዊው ግቢ በደማቅ ዝግጅት የቀረበውን የፎቶ ኤግዚቪሽን በቀጣይ ቀናትም መጎብኘት እንደሚቻል ተጠቅሷል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
















Comments