ለጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እውን መሆን ወጣቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ፡፡
- addis ketema Sub city
- May 27
- 1 min read
የካቲት 21-2017ዓም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዙሪያ ለክፍለ ከተማው ለብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሙሁራን አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ለጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እውን መሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ያሬድ ተፈራ ለጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ የወጣት አደረጃጀቶች ሚና የጎላ መሆኑን ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወጣት ያሬድ አክለውም ወጣቶች ከነጠላ ትርክት ይልቅ ለወል ትርክት ቦታ በመስጠት በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት እየተወጡት ያለውን ገንቢ ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው እኛ ወጣቶች ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማስቀደም በህብረ-ብሄራዊነት የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንደግፋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የአዲስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ገፆችን ይከተሉ!!










Comments