ለብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫዎች ስኬታማ አተገባበር የወጣቶች ክንፍ ጉልህ አሻራውን ይወጣል !
- addis ketema Sub city
- May 26
- 3 min read
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ አቅጣጫዎች አተገባበር ላይ የወጣቶች ክንፍ ሚና በሚል ርዕሰ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች እና አባላት ጋር መክሯል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መጋቢት ወር የለውጡ ቀያሽ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ኃላፊነት የተረከቡበት መሆኑን ጠቁመው በከተማችን በተከናወኑ በርካታ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች እንዲሁም በተመዝገቡት አመርቂ ውጤቶች የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የማስተባበር ሚናውን መወጣቱን ገልፀዋል። ወጣቶች በሰላም እና በልማት ስራዎች አያበረከቱት ከሚገኘው ጉልህ አሻራ መካከል በሀገር ህልውና ማስጠበበቁ የነበራቸውን ተሳትፎና ተጠናክሮ በቀጠለው የከተማችን ፈጣን ዕድገት ላይ እያሳረፉት የሚገኘውን ጉልህ አሻራ አቶ አለማየሁ ለአብነት ጠቅሰዋል። የአመለካከት እና የአስተሳሰብ ፈተናዎችን ፣ የውስጥ እና የውጭ ችግሮችን በመታገል ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸውን ያስረዱት አቶ አለማየሁ ከተሰራው በላይ ብዙ መስራት ስለሚጠበቅ ብልፅግና በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ያሳለፋቸውን አቅጣጫዎች አልቆ ለመከወን መረባረብ ይገባል ብለዋል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት ወጣት አክሊሉ ታደሰ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የፓርቲ አቅጣጫዎች ለሚከናወኑ የሰላም ፣ የልማት ፣ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ተግባራት የስራ መመሪያ መሆናቸውን ጠቅሰው ብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው ታሪካዊ ጉባዔው ያስቀመጣቸው ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ፣ ህብረብሔራዊ አብሮነትን ማጠናከር ፣ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ እና መሰል አቅጣጫዎች በውጤታማነት መፈፀማቸውን አስገንዝበዋል። ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው የነበሩትን ጥንካሬዎች የሚያጠናክሩ ፣ ጉድለቶችን የሚሞሉ ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ መንግስት እና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ፣ አብሮነትን የሚያጠናክሩ ፣ ፍትሀዊ ልማቱን የሚያጠናክሩ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ የልማት ፀጋዎች ፣ አኩሪ ታሪኮች ያሏት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ በመዝለቅም የነፃነት ቀንዲል መሆኗን ያመላከቱት ወጣት አክሊሉ ልዕልናዋን ለማረጋገጥ እየተደረገ ለሚገኘው ርብርብ ወረቶች መሆናቸውን ጠቃቅስዋል። የሀገረ መንግስት እና ብሔረ መንግስት ግንባታው መጓተት ሀገራችን ለገጠሟት ስብራቶች ምንጭ መሆኑን የጠቀሱት ወጣት አክሊሉ በመደመር ሀገር አሻጋሪ እሳቤዎች ፣ አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ትርክት ለማስረፅ አየተደረገ ባለው ጥረት ፣ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን እና በሌሎችም ትውልድ ላይ እየተሰሩ በሚገኙ ተግባራት ስብራቶች እየተጠገኑ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል። ድህነት ሌላኛው የሀገራችን ውስብስብ ችግሮች መንስኤ መሆኑን የጠቆሙት የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ የመልማት ፀጋዋን በአግባቡ ለመጠቀም በጀመረችው ብርቱ ትግል በግብርናው ፣ በቱሪዝም ፣ በማዕድን ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎችም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል። በታሪካዊ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያ ያመለጧትን ድሎች ለማስመለስ በሰጥቶ መቀበል መርህ ፣ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የወደብ ባለቤት ለመሆን አበረታች እንቅስቃሴዎች እየተደረገ እንደሚገኝ ያብራሩት ወጣት አክሊሉ ቅድሜያ ለጎረቤት ሀገር በሚል የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ተባብሮ ለማደግ እየተደረገ የሚገኘው ጥረትም ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቁመዋል። ውይይቱ ከኢኮኖሚ ፣ ከሰላም ፣ ከገዥ ትርክት ግንባታ እና ከሌሎችም አንፃር የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የድርሻውን ለመወጣት ተጨማሪ ግብአት የሚገኝበት መድረክ መሆኑን የጠቀሱት ወጣት አክሊሉ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ መሆኑንና እስከ ታችኛው መዋቅር ተደራሽ እንደሚሆንም አመላክተዋል ። የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በበኩላቸው በጠንካራ አቅጣጫዎችና በጠንካራ የአመራር ክትትል በየዘርፉ ለተመዘገቡ ድሎች የወጣቶች ክንፍ አመራርና አባላትም የማይተካ አሻራቸውን ማሳረፋቸውን አስረድተዋል። ብልፅግና በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ፣ ሀገርን የሚያሻግሩ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን የጠቆሙት ወጣት መለሰ ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ፣ የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን በማስረፅ ህብረ ብሔራዊ አብሮነትን ለማስረፅ የተጀማመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጣቶች ሚናችንን ልናልቅ ይገባል ብለዋል። ስራን የማማረጥ አመለካከትን በመቅረፍ ፣ ስራ ፈጣሪነትን በማጠናከር ያሉትን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ልማቱን ለማፋጠን ብልፅግና ያስቀመጠውን አቅጣጫ በማሳካት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ርብርቡን ማጠናከር እንደሚገባም ወጣት መለሰ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሰነድ አብራርተዋል። ህዝብን የሚያቀራርቡ ለሀገር ግንባታ ፋይዳ ያላቸው ጠንካራ የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አቅሙን በማስተባበር ተምሳሌታዊ ሚናውን ሊያጠናክር እንደሚገባ ተገልጿል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍን ተቋማዊ ሚና በማጎልበት ለብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫዎች ስኬታማ አፈፃፀም እና ለሁሉም የከተማችን ወጣቶች ተጠቃሚነት የጀመሩትን ርብርብ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የውውይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት











ገዢ ትርክት