top of page

“ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለሀገር ብልፅግና”

በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣት ክንፍ አስተባባሪነት የብዝሀ ቋንቋ ትምህርት ለወጣት ክንፍ ስራ አስፈፃሚ ና የህብረት አመራሮች ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተከናወነ። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣት ክንፍ ኃላፊ ወጣት ያሬድ ተፈራ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ ነው ስንል ብዝሀ ማንነትን በአግባቡ ተረድቶ ተግባራዊ ስለሚያደረግ ነው ያሉ ሲሆን አክለውም ቋንቋ መግባቢያ ብቻም ሳይሆን መቀራረብንና ፍቅርንም ስለሚያዳብር ወጣት አባላት ይህን ትምህርት አጠናክረው መማር እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ትምህርቱ ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚቀጥል ሲሆን በዚህም የኦሮምኛና የትግርኛ ቋንቋ ትምህርት በክፍለ ከተማው የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ወጣት አባላት የሚሳተፉ ይሆናል።


 
 
 

Комментарии


bottom of page