ሃገሬን እገነባለሁ ሃላፊነቴን እወጣለሁ!!
- addis ketema Sub city
- May 26
- 1 min read
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ "ሃገሬን እገነባለሁ ሃላፊነቴን እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄደ።
በደም ልገሳዉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ የሆኑት ወጣት ያሬድ ተፈራ ዉድ የሆነዉን የሰዉ ሂወት ማዳን የህሊና እርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ ወጣቶች ይሄ በጎ ተግባር በማስተባበርና ደም በመለገስ ለሚያደርጉት አስተዋፆኦ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩም ላይ የብልፅግና የወጣቶች ክንፍ አባላት፣የወረዳ ዘርፍ ሰብሳቢዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ሚያዝያ 25/2017ዓ.ም










Comments