top of page

ሀገሬን እገነባለሁ ሀላፊነቴን እወጣለሁ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ በተለያዩ ወረዳዎች "ሀገሬን እገነባለሁ ሀላፊነቴን እወጣለሁ በሚል መሪ ቃል የጋራ ውይይት መካሄዱ ተገለፀ።

 ወጣቶች በሀገር ግንባታ ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ "ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ" በማለት ሀገራቸውን ከማንኛውም የችግር ምንጭ በመከላከልና የሀገርን ሰላም በማፅናት እንዲሁም ሀገረ-መንግስታቸውን በተሻለ መንገድ በመገንባት በአንድነትና በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዞ ወደ ብልፅግና ማማ መድረስ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በስተመጨረሻም የመወያያ ሰነዱ ከቀረበላቸው ወጣቶች ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ከመድረኩ በቂ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የጋራ መግባባት ደርሰው ውይይቱን አጠናቀዋል።

prosperity party logo

 
 
 

Comments


bottom of page